Fines Victoria

Primary content

Download as a PDF fileይህ ጠቃሚ መረጃ ነው። ለዚህ መረጃ ካልተረዳዎት ወይንም ስለርስዎ ቅጣት የሆነ ሰው ለማነጋገር ከፈለጉ ለቪክቶሪያ ቅጣት/ Fines Victoria በስልክ (03) 9200 8111 ወይም 1300 369 819 (በክልላዊ ስልክ ጥሪዎች ) መደወል እና በሚፈልጉት ቋንቋ አድርጎ የሆነ ሰው ሊያነጋግርዎት ይችላል።. 

 

የቪክቶሪያ ነዋሪ ቅጣት አሰራር ዘዴ

ቅጣት ማለት ህጉ በሚጣስበት ጊዜ የሚሰጥ የገንዘብ ቅጣት ነው። የቅጣቶቹ ዓላማ ለማህበረሰቡ ደህንነት ለመርዳትና ህገወጥ የሆኑ ባህሪዎች እንዳይፈጸሙ በማበረታታት ህዝባዊ ትእዛዝ ለማስቀመጥ ነው።

ዋና የገንዘብ ቅጣቶች ዓይነት የስምምነት ህግን በመጣስ ቅጣቶችና የፍርድ ቤት ቅጣቶች ናቸው።

  • ለስምምነት ህግ በመጣስ ቅጣቶች የሚካሄደው በአስገዳጅ ድርጅቶች እንደ የአካባቢ ምክር ቤቶች እና የቪክቶኢያ ፖሊስ ያሉት ነው። በአብዛኛው የሚሰጡት ቅጣቶች ለቀላል ወንጀል ጥፋቶች ማለት እንደ የትራፊክ ህግ መጣስ እና የመኪና ማቆሚያ ህግን መጣስ ይሆናል። አንድ ሰው በቀረበበት ወንጀል ጥፋት ወደ ፍርድ ቤት መሄድ ሳያስፈልግ ወይም ለጥፋቱ በማመን የገንዘብ ቅጣቱን በመክፈል ማጠናቀቅ ይቻላል።
  • ለፍርድ ቤት ቅጣቶች ይህ በወረዳ ፍርድ ቤት ወይም በዳኛ በኩል የሚሰጥ ማስገደጃ ይሆናል።

የገንዘብ ቅጣት ደርስዎት ከሆነ

ስላለዎት የገንዘብ ቅጣት በቀጥታ የሆነ ነገር ማካሄዱ ጠቃሚ ነው። ምንም ነገር ካላካሄዱ ግን የቅጣቱ መጠን እየጨመረ ስለሚሄድ መጠኑ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ይደርሳል።

ያለዎት ምርጫዎች እነዚህ ናቸው:

አሁን መክፈል ያለዎትን ቅጣት በኦንላይን መስመር ላይ በቀጥታ ለመክፈል በድረገጽ fines.vic.gov.au ላይ መግባት።

በየጊዜ መደበኛ ክፍያዎችን ማካሄድ አሁን ሁሉንም መጠን ለመክፈል አቅም ከሌለዎት፤ ቀስ በቀስ እንደ አቅምዎ ለመክፈል ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ። በሴንተርሊንክ እርዳታ የሚያገኙ ከሆነ ካለዎት ክፍያ እየተቀነሰ እንዲከፈል እኛን መጠየቅ ይችላሉ። በቀጥታ በአካውንት ክፍያን ለማስገባት በድረገጽ፡ online.fines.vic.gov.au/Pay-by-instalments ላይ መግባትና የኦንላይን መስመር ቅጽን መሙላት።

የክፍያ ጊዜ እንዲራዘም መጠየቅ የክፍያ ጊዜን ለማራዘም በድረገጽ online.fines.vic.gov.au/Payment-extension ላይ መግባትና በኦንላይን መስመር ቅጹን መሙላት።

የሆነ ሰው እየነዳ ከነበረ ቅጣት መረቀቱ በራስዎ አድራሻ መልእክቱ ከመጣ ነገር ግን በዚያን ጊዜ መኪናውን የሚነዱ ካልነበሩ እና በዚያን ጊዜ ይነዳ ለነበረው ሰው ለማስታወቅ ይችሉ ይሆናል። ስለዚህ የቅጣት ወረቀቱ ለርስዎ ሳይሆን ለነዚያ ሰዎች ይላካል። ሹፌሩን ለማሳወቅ በድረገጽ online.fines.vic.gov.au/Nominate መግባትና በቅጹ ላይ መሙላት። ቅጹ ተቀባይነት ስለማግኘቱ ለማረጋገጥ በተቻለ ፍጥነት ይህንን ማድረግ አለብዎት።

በቤተሰብ ሁከት ፈጠራ ችግር ከነበረብዎት – የቤተሰብ ሁከት ፈጠራ በደረሰብዎት ምክንያት ይህንን የህግ መጣስ ቅጣት ካገኙ ለቤተሰብ ሁከት ፈጠራ አሰራር ማመልከት ይችላሉ። ለዝርዝር መረጃ በድረገጽ fines.vic.gov.au/fvs ላይ ገብቶ ማየት። 

ላለዎት የህግ መጣስ ቅጣትን ለመዝጋት መስራት ከፈለጉ በሥራና በልማት የፈቃድ አሰራር በኩል አንዳንድ እንቅስቃሴ ሥራዎችና ህክምናዎችን በማካሄድ ያለዎትን ቅጣቶች ለመዝጋት መሥራት ይችሉ ይሆናል። ለከባድ ችግር ከተጋለጡና ጥቅም የልሽ መሆን (መጠለያ ቤት የለሽ፤ የአእምሮ ህመም፤ የቤተሰብ ሁከት፤ የአልኮሆል ወይም የአደገኛ እጽ ሱሰኛ ከሆኑ) ይህ ለርስዎ አማራጭ ሊሆን ይችላል። ለበለጠ ዝርዝር መረጃ በድረገጽ፡ justice.vic.gov.au/wdp ላይ ገብቶ ማየት። 

ለተቀረጸ ፎቶግራፍ ማየት ከፈለጉ – ለፍጥነት አነዳድ ቅጣት እና ለቀይ የትራፊክ መብራት መጣስ ቅጣት ያነሳነው ፎቶዎች። ስእሉን ተጭኖ ለማውጣት በድረገጽ online.fines.vic.gov.au/View-image ላይ ገብቶ ማየት። 

ለርስዎ ህግ ጥሰት ቅጣት እንደገና ማየት አለብን ብለው ካሰቡ

ላለዎት ቅጣት እንደገና ግምገማ እንዲደረግ መጠየቅ ይችሉ ይሆናል፤ ይህም:

  • የተሰጠዎት ቅጣት ውሳኔ ህገወጥ ነው ብለው ካሰቡና ቅጣት ማግኘት የለብኝም ብለው ካመኑበት
  • ስህተት የሆነ ነገር ካደረጉ፤ ነገር ግን ይህን ህግ ለመጣስ ለየት ያለ ምክንያት ካለዎት
  • ቅጣቱ ለርስዎ በስህተት ተሰጥቶ ከነበር እና ይህ ለሌላ ሰው መሰጠት እንደነበረበት እንጂ ለርስዎ እንዳልነበር
  • ስለ ቅጣቱ ምንም የማያውቁ ከነበር – በሀላፊው በኩል ለርስዎ መላክ ወይም መሰጠት ካልነበረበት
  • ለየት ያሉ ሁኔታዎች ከነበረብዎት – መጠለያ ቤት የለሽ፤ የአእምሮ ህመም፤ የቤተሰብ ሁከት፤ የአልኮሆል ወይም የአደገኛ እጽ ሱሰኛ ከሆኑ

ከነዚህ ውስጥ አንደኛው ተግባራዊ ከሆነ ቅጣቱ እንደገና እንዲታይ መጠየቅ ይችላሉ። በድረገጽ online.fines.vic.gov.au/Request-a-review ላይ መግባትና በኦንላይን መስመር ቅጽን መሙላት። ለእኛ ማረጋገጫ የሚሆን ለተናገሩት ማስረጃ መስጠት አለብዎት።

ማሳሰቢያ: በፍርድ ቤት ዳኛ ቅጣቱ ከተሰጥዎትና በፍርድ ችሎቱ ላይ ካልተገኙ፤ የበለጠ መረጃ ከፈለጉ ለፍርድ ቤቱ መጠየቅ ያስፈልጋል። በፍርድ ቤት ዳኛ የተሰጠው ውሳኔ እንደገና እንዲታይልዎት ወይም ሌላ አማራጭ ካለዎት ለማወቅ ከፈለጉ መጠየቅ ያስፈልጋል። ለፍርድ ቤቱ ከማነጋገርዎት በፊት ህጋዊ የሆነ ምክር እርዳታ ማግኘት አለብዎት – ለአካባቢዎ ማህበረሰብ ህጋዊ የሆነ ማእከል ለማግኘት በድረገጽ www.fclc.org.au ላይ ገብቶ ማየት ወይም በስልክ (03) 9652 1500 አድርጎ መደወል።

ስላለዎት ቅጣት ምንም ነገር ካላደረጉ

ህግ በመጣስ ቅጣት

የቅጣት ማሳሰቢያ ወረቀት በህግ አስገዳጅ ድርጅቶች ይሰጣል እንዲሁም በተወሰነው ጊዜ ውስጥ መክፈል አለብዎት።

ለቅጣት ማሳሰቢያ ወረቀት ካልከፈሉት ተጨማሪ የቅጣት ማሳሰቢያ ወረቀት ይመጣል። በዚህን ጊዜ የቅጣቱ ክፍያ ዋጋ ይጨምራል። ቅጣቱ መክፈል አለብዎት ወይም ስለሚኖርዎት ምርጫዎች ከቅጣት ወረቀት አቅራቢ ድርጅት ጋር መነጋገር አለብዎት። የእነሱ ስልክ ቁጥር በማሳሰቢያ ወረቀት ጀርባ ላይ ይገኛል።

አሁንም ስለ ቅጣቱ ምንም ነገር ካላደረጉ የመጨረሻ መጠየቂያ ማስጠንቀቂያ እንደሚመጣ እና የቅጣቱ ዋጋ መጠን ከፍ ያለ ይሆናል። ይህንን ቅጣት በተወሰነው ቀን ውስጥ መክፈል አለብዎት ወይም እኛን በድረገጽ fines.vic.gov.au/contact-us ማነጋገር።

አሁንም ስለ ቅጣቱ በተመለከተ ምንም ነገር ካላደረጉ:

  • የርስዎ መንጃ ፈቃድ ወይም የመኪና ታርጋ ምዝገባ ሊታገት ይችላል
  • ከርስዎ ባንክ ወይም ደመወዝ ገንዘብ ሊወሰድ ይችላል
  • በርስዎ ስም የፍርድ ቤት ማዘዣ ሊወጣ እንደሚችልና የቅጣት ክፍያ መጠኑ ከፍ ያለ ይሆናል። ከዚህ ጊዜ በኋላ የፖሊስ መኮንን/Sheriff ተሳትፎ ሊያደርግ ይችላል። ለምሳሌ፡ የፖሊስ መኮንን መኪናዎን ወስዶ መሸጥ ይችላል።

በፍርድ ቤት ቅጣት
በፍርድ ቤት ውስጥ ባለ ዳኛ ወይም ማጅስትረት በኩል ቅጣት ከተሰጥዎት ይህ የፍርድ ቤት ቅጣት ይባላል። በፍርድ ችሎት ቀን ያለዎትን ቅጣት ካልከፈሉት፤ የፍርድ ቤት ቅጣት መሰብሰቢያ መግለጫ ጽሁፍ ወረቀት/(CFCS) በቪክቶሪያ ቅጣት/Fines Victoria በኩል ይሰጣል። የ CFCS በሚደርስዎት ጊዜ በጽሁፍ መግለጫ ወረቀቱ ላይ በተዘረዘረው የክፍያ ቀን (ቀናት) ቅጣቱን መከፈል አለብዎት።

ለቅጣት ክፍያው ቀስ በቀስ ለማስገባት መጠየቅ ይችላሉ ወይም ለመክፈል የበለጠ ጊዜ እንዲሰጥዎ መጠየቅ ይችላሉ። እኛን ለማነጋገር ድረገጽ fines.vic.gov.au/contact-us

እንዲሁም በርስዎ CFCS ውስጥ ስለርስዎ ቅጣት ጠቃሚ የሆኑ ሌሎች መረጃዎችን ያካትታል። ስለርስዎ CFCS ካልተረዳዎት በተቻለ መጠን እኛን ማነጋገር እንዳለብዎት ነው ድረገጽ fines.vic.gov.au/contact-us

ስለ ፍርድ ቤት ቅጣት በተመለከተ ምንም ነገር ካላደረጉ:

  • የርስዎ መንጃ ፈቃድ ወይም የመኪና ታርጋ ምዝገባ ሊታገት ይችላል
  • ከርስዎ ባንክ ወይም ደመወዝ ገንዘብ ሊወሰድ ይችላል
  • በርስዎ ስም የፍርድ ቤት ማዘዣ ሊወጣ እንደሚችልና የቅጣት ክፍያ መጠኑ ከፍ ያለ ይሆናል። ከዚህ ጊዜ በኋላ የፖሊስ መኮንን/Sheriff ተሳትፎ ሊያደርግ ይችል ይሆናል። ለምሳሌ፡ የፖሊስ መኮንን መኪናዎን ውስዲ መሸጥ ይችላል።

ስለ የፖሊስ መኮንን/Sheriff

የፖሊስ መኮንን/ Sheriff በቪክቶሪያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን ያለው ለሚከተሉት የፍርድ ቤት ማስገደጃ ለመስጠት ሃላፊነት አለው:

  • በቪክቶሪያ ቅጣት/Fines Victoria የተመዘገበን ያልተከፈለ ቅጣት ማስገደድ
  • በፍርድ ቤት ዳኛ ወይም ማጅስትረት የታዘዘን ያልተከፈለ ቅጣት ማስገደድ ይሆናል።

በርስዎ ቅጣት ላይ ምንም ካላደረጉና ችላ ካሉት የፍርድ ቤት ማስገደጃ ወረቀት በርስዎ ላይ ሊሰጥ ይችላል።

በርስዎ ላይ ስለቀረበ የፍርድ ቤት ማስገደጃ ወረቀት ለመነጋገር የፖሊስ መኮንን ሀላፊዎች ወደ ቤትዎ ወይም ሥራ ቦታ ላይ መምጣት ይችላሉ፤ ወይም መንገድን በመዝጋት ማስቆም ይችሉ ይሆናል። እንዲሁም የፖሊስ መኮንን ሀላፊዎች ለርስዎ ተሽከርካሪ ጐማን እንዳይንቀሳቀስ መቆለፍ/ማጣበቅ ይችላሉ።

ለፖሊስ መኮንን ሀላፊዎች መፍራት የለብዎትም። የሚመጡት ስላልተከፈለ ቅጣትዎ ቅንጅት ለማድረግ መርዳት ስለፈለጉ ሲሆን በክብር ያስተናግዳሉ። ያለዎትን ምርጫዎች በማብራራትና ምን ማድረግ እንዳለብዎት እንዲረዳዎት ያደርጋሉ።

አስፈላጊ ከሆነ የፖሊስ መኮንን ሀላፊዎች ስልጣን የሚኖራቸው:

  • ንብረትን እንደ የርስዎ ተሽከርካሪ ያለን ፈልጎ ማግኘት፤ ለመሸጥ
  • ለርስዎ ተሽከርካሪ ጎማን መቆለፍ ወይም ማገድ
  • እርስዎን ማሰር እና ወደ ወረዳ ፍርድ ቤት ማቅረብ።
Return to the top